አገልግሎት

አገልግሎት

ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር እሁድ ፣ በዓበይት በዓላት ፣ በየወሩ ለቅዱስ ሚካኤል በዓል… ከምትሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ የክርስትና ፣ የሥርዓተ ጋብቻ ፣ የፍትሃት እንዲሁም የምክር አገለግሎት ከዓመት እስከ ዓመት ትሰጣለች።

ከላይ የተዘረዘሩትንም ሆነ ሌሎች አገልግሎቶችን ለመጠቀም ቀደም ብሎ በስልክ ወይም በአካል ማሳወቅ ያስፈልጋል። ይህም የሚያስፈልገውን ዝግጅት ለማድረግ እንዲሁም በቂ ትምህርትና የምክር አገልግሎት ለመስጠት /ለማድኘት ያስችላል። በተለይም ለአዋቂ ተጠማቂዎች እና ጋብቻቸውን በቤተ ክርስቲያን ለመፈጸም ለሚሹ ሰፋ ያለ ትምህርት ስለምያስፈልጋቸው ምሥጢራቱን ሊፈጽሙ ካቀዱበት ጊዜ ቢያንስ አንድ ወር ቀድመው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

Contact us @ 317-332-4898 OR 317-636-7670

፩. ዘወትር እሁድ ፡- ከ 5:00 AM ጀምሮ እስከ 12:00 PM

  • ስብሐተ ነግህ ኪዳን ቅዳሴ መዝሙርና የትምህርተ ወንጌል አገልግሎት ይሰጣል።

፪. በየወሩ :-

  • በ12 ለቅዱስ ሚካኤል
  • በ21 ለእመቤታችን
  • በ27 ለመድኃኔዓለም
  • በ29 በበዓለ ወልድ

እንዲሁም በዓበይት በዓላት በእለቱ (ከሰኞ አስከ እስከ ቅዳሜ) ከ 8:00 AM እስከ 10:00 Am :-

  • ይታጠናል ፣ ጸሎተ ኪዳን ይደርሳል ፣ ተአምር ፣ ድርሳን ይነበባል።

፫. በየወሩ ለቅዱስ ሚካኤል በዓል በእለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ይካሄዳል። እንዲሁም በየወሩ ለቅዱስ ሚካኤል በዓል በሚቀርበው ቅዳሜ ከ4:00 PM እስከ 6:00 PM ወርሃዊ የወንጌል ጉባኤ ይደረጋል።
በእለቱም

  • የሰርክ ጸሎት ይደርሳል
  • መዝሙራት ይቅርባሉ
  • የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ይሰጣል።

፬. ከእሁድ በተጨማሪ ካህናት አባቶችን በግል ለማነጋገር ወይም የምክር አገልግሎት ለማግኘት ለሚፈልጉ በቀጠሮ ይስተናገዳሉ።
ለበለጠ መረጃ :-
በ (317) 636-7076 ወይም (317) 916-0298 ይደውሉ::